እንደ ተሰቀለ ሆነህ ነበር በፊቴ ተስለህ ዛሬ ሌላው ጋርዶብኛል አንተን ማየት ተስኖኛል ፊቴን ላዙር ወደ መስቀልህ አንደገና በፊቴ ልሳልህ ልቤን ልስጥህ የህይወቴን መውጫ እየሱሴ ሁንልኝ ማምለጫ 1 አይኖቼ ተጋርደው ክብርህን እንዳላይ ከፊትህ እርቄ የቤትህ ውስጥ ኮብላይ ላንተ ኢየዘመርኩኝ ወደውጭ አያለው አካሌ ቤት ውስጥ ልቤ ግን ደጅ ነው በመንፈስ ጀምሬ እንዳልጨርስ በሥጋ ጌታዬ ሆይ ሳበኝ ወዳንተ ልጠጋ (2*) 2 የምህረት ደጅህ አልተዘጋም ገና በእግሮችህ ስር ልውደቅ እፊትህ ልምጣና በደምህ እጠበኝ እስክነፃ ድረስ የጠፋኝ ውበትህ ዳግም እስኪመለስ በፀጋህ ደግፈኝ ራራልኝ ጌታዬ አንተ ባለህበት ይሁን ፍፃምዬ (2) ፊቴን ላዙር