Song Lyrics

በፍቅርህ መልህቅ

Adane Mathewos
Special Edition
በፍቅርህ መልህቅ እኔ ተጣብቄ መልካምነትህን ጠንቅቄ አውቄ ምንም አያጓጓኝ አልሆነብኝ ራቤ ኢየሱስ አንተው ነህ የእውቀትና የጥበብ መዝገቤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረ ለእኔ ግን የተገለጠው በእኔ ውስጥ መሆንህ ነው ይሄ ነው የበራልኝ >> ደሰ የምያሰኘኝ >> የተገለጠልኝ >> ያስደነ'ከኝ ለተሻለ ኪዳን ለርስቱ የተለየ ወገን በፈሰሰው ደምህ ሆኛለው የንጉሥ ካህን በዘመኑ ፍጻሜ ያለ ሥጋት በነፃነት እንድኖር አብ ካሰየኝ ፍቅር አይኖረኝም የሚበልጥ ክብር ተማርኪያለው ባንተ እኔ ተሸንፌያለው ከማይጠፈው ዘር በመንፈስ ተወልጃለው ካንተ ውጭ የለም በልቤ የሾምኩት ንጉሥ በሕይወቴ ተሞገስ የነፍሴ ጌታ ኢየሱስ ካንተ ጋር የዋሉ ከእጅህም በልተው የለመዱ እውነቱን ስትገልጠው ጠፉ ሁሉም እያጎረመረሙ ከሚጠፋው ዓለም ርቆ ለተከተለህ ፊትህን ለሚሻው ጴጥሮስም በእምነት አንተን ነው የሕይወት ቃል ኣለህ ያለው እኔም አሃ ለማያልፈው ለዘላለም ኑሮዬ ብዬሃለው አንተን ብቻ የሕይወት እንጀራዬ የማትርቅ የማትጠፋ ሁሌ ከአጠገቤ እውነት ሕይወት መንገዴ ገበተኻል በልቤ አብን የተረክልኝ መንፈስህን የሰጠኸኝ ምንም እስከ ማይገርመኝ ድረስ ያስደነከኝ አንተው ነህ ጌታዬ ለራስህ የለየኸኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection