Song Lyrics

ስጋት የሌለበት

Abenezer Debebe
Special Edition
ካንተ የሚበልጥ ምን አለና ወዴት እንሄዳለን ጌታ ካንተ የሚሻል ምን አለና ወዴት እንሄዳለን ጌታ አንተ የህይወት ቃል አለህ የዘለዓለም ምንጭ ነህ ኢየሱስ የህይወት ቃል አለህ የዘለዓለም ምንጭ ነህ ስጋት የሌለበት መኖሪያ አገኘች ነፍሴ ሰላም የሞላበት ማረፊያ አገኘች ነፍሴ ለምድራዊ ነገር አልተከተልኩህም ታይቶ ለሚጠፋው ወደ አንተ አልቀረብኩም ህይወት ካንተ ወዲያ ከቶ ስለሌለ ይኸው መጥቻለው አንተ ዘንድ ስላለ እውን ይሆናል ባዶነቴ ፈፅሞ አይሞላም ካላንተ ህይወቴ የመኖሬ ትርጉም አንተ ነህ ኢየሱስ ልቤ ያረፈብህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection